ይህ የትምህርት መርሐግብር የቤተክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት (ዶግማ) ለምዕመናን በያሉበት ለማድረስ የተዘጋጀ የትምህርት መርሐግብር ነው።

ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የማይጠይቅ እና በየትኛውም ደረጃ ያሉ ምዕመናን በነፃ እንዲከታተሉት ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። መርሐግብሩ በተለያዩ መምህራን የተዘጋጁ የዶግማ ኮርሶችን የሚይዝ ይሆናል። ለአብነትም፦

  • የነገረ ሃይማኖት መግቢያ
  • አዕማደ ምሥጢር
  • የነገረ ድኅነት መግቢያ
  • እና ሌሎችም
ትምህርቱን በመከታተል መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ ለማወቅ እንጣር!

በመምህር ህሊና በለጠ
በዚህ ኮርስ፣ ነገረ ሃይማኖትን ለምን ማጥናት እንደሚገባን ዓላማውን እና ጥቅሙን እናያለን፤ የሃይማኖንትን ምንነት እናጠይቃለን፤ ስለ ነገረ እግዚአብሔር እናነሳለን፤ ስለ ሥነፍጥረትም ዳሰሳ እናደርጋለን፤ በስተመጨረሻም የነገረ ሃይማኖትን ትምህርት ምንጮች በማንሳት ኮርሱን እንቋጫለን።

በ መጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ማናዬ