የማኅበረ ቅዱሳን ኢለርኒንግ ፕላትፎርም በይፋ ሥራ መጀመሩ በነሐሴ 15 ቀን 2014ዓ/ም ተበስሯል።
በማኅበረ ቅዱሳን ኢለንሪኒንግ ፕላትፎርም የርቀት ትምህርት ኮርሶችን እና ነበጻ የሚሰጡ ኮርሶችን መከታተል ይቻላል።
ማኅበሩ በነሐሴ 15፣ 2014 ዓ/ም ሦስት ደረጃዎች ያሉት የርቀት ትምህርት መርሐግብር ይፋ አድርጓል።
በአሁኑ ሰዓት የመሠረታዊ ርቀት ትምህርት መርሐግብር በ17 የማኅበረ ቅዱሳን ማዕከላት፣ በአንድ ሰ/ት/ቤት እንዲሁም በኦንላይን አማራጭ እየተሰጠ ይገኛል።
የመሠረታዊ ርቀት ትምህርት መርሐግብር ዝግጅት የተጀመረው በ3 ቋንቋዎች ሲሆን አሁን ላይ የአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ሞጁሎች ታትመው አገልግሎት ላይ ናቸው፤ የትግርኛ ሞጁሎች ዝግጅትም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ማንኛውም አካል የኢሜይል አድራሻውን በመጠቀም፣ በራሱ ተመዝግቦ የነፃ ትምህርቶችን መከታተል ይችላል።
የርቀት ትምህርት ለመከታተል ትምህርቱን በጀመሩ ማዕከላት ወይም በኦንላይን አማራጭ ለመማር በዚሁ መካነ ድር በሚገኝ ቅጽ ቅድመሁኔታዎችን አሟልቶ መመዝገብ ያስፈልጋል።
የርቀት ትምህርት መርሐግብርም ሆነ በንፃ የሚሰጡ ኮርሶች ለማንኛውም እምነት ተከታዮች ክፍት ናቸው።